በውል ውስጥ የስራን ግዴታ ሳይወጡ ሌላው ወገን ግዴታን አልተወጣም የሚል ክስ ማቅረብ ይችላል?

በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1757 ላይ በግልፅ እንደተደነገገው አንድ ውል እንዱፈፀምለት የ+ሚጠይቅ አካል መጠየቅ የሚችለው በውሉ መሠረት አስቀድሞ ሲወጣው የሚገባግዴታ ካለ ይህንን ግዴታ ከተወጣ በኋላ መሆኑን ነው፡፡ 

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተጀመረ ክርክርም ይህን የሳያል ጉዳዩ የነበረው በከሳሽ ወኪል በኩል ለተከሳሽ በብር 50,000 ብር የሰጡላቸው መሆኑን ለቅድሚያም 19,000 ብር ከፍለውኝ መኪናውን አስረክቤያቸዋለሁ፡፡ ነገር ግን ጠሪውን 31,000 ብር ከፍለው መኪናውን በስማቸው እንዲዞሩ ተከሳሹን ብጠይቃቸው ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ተገደው እንዲያዞሩ ይደረግልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡ 

ተከሳሹም በሰጡት መልስ በሽያጭ ውሉ ውስጥ መኪናው ሽያጭ ቀሪ ገንዘብ ይስጡኝ ማለታቸው ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡ 

የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በውሉ ላይ እንደተመለከተው ተከሳሽ ግዴታቸውን እንዳልተወጡና በዚህም ሁኔታ የመኪናው ሽያጭ ቀሪ ገንዘብ ይከፈለኝ ጥያቄ ማንሳታቸው ተቀባይነት እንደሌለው በመወሰን የተከሳሽን ክስ ሰርዞታል፡፡ ይግባኝ የተባለለት ፍ/ቤትም ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሠረት ሰርዞታል፡፡ 

ክርክሩም ሰበር ችሎት ድረስ ይግባኝ በመባሉ ችሎቱ ጉዳዩን አግባብነት ካላቸው ህጐች ጋር በማገናዘብ ተመልክቶታል፡፡ ግራቀኙ ወገኖች አደረጉት በተባለው የመኪና ሽያጭ ውል ውስጥ የካምቢዮ ብልሽተ እንዳለውና ይህን የሚሰራት ወይም የመተካት ግዴታ እንዳለባቸው ተመልክቷል፡፡ የመናውን ካምቢዮን አሰርተው መክናውን ለተጠሪው ስለ ማስረከባቸወ የሚገልፅ ማስረጃ አመልካቹ አላቀረቡም፡፡ ተጠሪው መክናውን ተረክበው በእጃቸው ማስረከባቸው ብቻ ይህንን ሊያስረዳ አይችልም፡፡ 

ስለሆነም የስር ፍ/ቤቱ አመልካቹ የመኪናው ካምቢዮን የማስተካከል ግዴታቸውን ላይወጡ የቀሪ ገንዘብ ክፍያ ማንሳት አይችሉም በማለት ከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ አግባብነት አለው በማለት አፅንቶታል፡፡

ስለዚህ አንድ ውል የተዋዋለ አካል ውሉ ላይ የተቀመጠውን ግዴታ ሌላኛወገን እንዲፈፅምከመጠየቁ በፊት አስቀድሞ የራሱን ግዴታዎተ መፈፀም እንዳለበት ከዚህ እንረዳለን፡፡ 

ተጨማሪ ጥያቄ አስተያየት ቢኖርዎት ያነጋግሩን ይጠይቁን

ኢሜይል  ፡-[email protected]

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የዉል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፍቺ ጠበቃ… ማግኘት ይችላሉ፡፡

Scroll to Top