የስራ መሪ መደብ ላይ በጊዜያዊነት መስራት ግለሰቡን የስራ መሪ ከመባል ያስቀረዋል?

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 377/1993 አንቀጽ 3(2)(ሐ) በግልፅ እንደተቀመጠው በስራ መሪ ላይ ለተቀመጠ ሰው አዋጁ ተፈፃሚነት እንደሌለው ያሳያል፡፡ ነገር ግን በስራ መሪ ምድብ ላይ በጊዜያዊነት መቀመጥም ተመሳሳይ የሆነ የህግ ውጤት ይኖረዋል ማለት ነው? 

ጉዳዩ በአመልካች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በተጠሪ በአቶ ሙላት ታረቀኝ መሃከል ሲሆን ተጠሪ ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከ1972 ጀምሮ ተቀጥረው በአመልካች ድርጅት ውስጥ የተለያዩ ስራ ሲሠሩ ቆይተው ሃላፊነትህን አልተወጣህም በሚል ምክንያት አለአግባብ ስላሰናበቱኝ ፍ/ቤቱ የስራ ስንብቱን ውድቅ እንዲያደርጉልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡ 

የፌደራል መጀመሪያ ፍ/ቤትም ተጠሪ የስራ መሪ መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል፡፡ 

ተጠሪም ይግባኙን ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱም ተጠሪ ምክትል የግምጃ ቤት ሃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ነገር ግን ይህንን የመሪነት ስፍራ በመያዝ ያገለገሉት በጊዜያዊነት ስለሆነ በቋሚነት ተመድበው ያልሰሩበት የስራ መደብ የስራ መሪ ሊያሰኛቸው አይችልም በማለት የስር ፍ/ቤቱን ውሳኔ ሽሮታል፡፡ 

የሰበር ሰሚ ችሎትም ተጠሪ በስራ መደቡ ይሰራ የነበረው በቋሚነት ሳይሆን በተጠባባቂነት መሆኑ ተጠሪን ሰራተኛ ያሰኘዋል ወይስ አያሰኘውም የሚለውን ነጥብ ይዞ ጉዳዩን መርምሮቷል፡፡ ተጠሪ በተጠባባቂነት ተመድበው ሲሠሩ ለቦታው የሚገባውን ጥቅማጥቅም የሚያገኙ እንደነበርና በስራው ሙሉ ሃላፊነት ወስደው ይሰሩ እንደነበር ተገልፂል፡፡ በአዋጅ ጥር 494/1998/ በተደረገው ማሻሻያ መሰረት የስራ መሪ ማለት በቋሚነት ብቻ ሳይሆን በአሠሪው በተሰጠው ውክልና መሠረት በአዋጅ የተዘረዘሩትን ተግባራት የሚያከናውን ነው፡፡ ይህንን መስፈርት ደግሞ ተጠሪ ስለሚያሟሉ የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሳኔ አግባብነት የለውም በማለት ሽሮታል፡፡ 

አንድ ሠራተኛ በስራ መሪ መደብ ላይ ተመድቦ ይሰራ የነበረው በተጠባባቂነት መሆኑ ብቻ ያሰው አሰሪ ሳይሆን ሠራተኛ ነው በሚለው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም፡፡ ስለዚህም በእንደዚህ አይነት ስፍራ ላይ ላለ ሰው የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 377/96 ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ስለሆነም አንድ ሰራተኛ በጊዜያዊነትም ቢሆን የሰራበትን የስራ መደብ የስራ መደቡ እንደሆነ አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ 

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን 

ኢሜይል  ፡-[email protected]

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ… ማግኘት ይችላሉ፡፡

Scroll to Top