የስራ ውሉ ከህግ ውጪ ሲቋረጥ ሊከፈሉ የሚገባቸው ክፍያዎች

አንድ ሠራተኛ የስራ ውሉ የተቋረጠው ህገወጥ በሆነ መንገድ ነው ብሎ ፍ/ቤቱ ከወሰነ ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ የሚገባው ከህግ ውጪ የሆነ የስራ ውል ማቋረጥ የሚያስከትላቸው ውጤቶችን የሚገዛውን የህጉን ዘርፍ ባገናዘበ መልኩ መሆን አለበት፡፡ 

በሰበር ችሎት የታየ መዝገብም ይህንን ያስረግጣል፡፡ ጉዳዩ በአመልካች በአቶ ኩምሳ በጅሳ እና በተጠሪ በብሔራዊ አስጐብኚና ወኪል ድርጅት ሲሆን አመልካች ላለፋት 24 አመታት በሹፌርነት ሙያ ማገልገላቸውና ተጠሪም ያለ አግባብ የስራ ውሉን በሚቋረጡ አስፈላጊ ክፍያዎች ሁሉ እንዲከፈላቸው አመልክተዋል፡፡ 

ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍ/ቤትም የስራ ውሉ ያለአግባብ ኑው የተቋረጠው የሚል ድምዳሜ ላይ ቢደርስም እንዲከፈሉ የወሰናቸው ክፍያዎች ግን የ14 ቀን ደመወዝ ይህ ክፍያ ለዘገየበት ደግሞ የሁለት ወር ደመወዝ እንዲከፈላቸው እና የስንብት ወይም የጡረታ መብት ለአመልካች ካልተፈፀመ አቤቱታ የማቅረብ መብታቸውን ጠብቆላቸዋል፡፡ አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌ/ከ/ፍ/ብት ሲያቀርቡም ይግባኛቸው ተሰርዞባቸዋል፡፡ 

ሰበር ችሎት እንደተገነዘበውም በስር ፍ/ቤቶች የስራ ስንብቱ ህገ ወጥ መሆኑ ተገለፆ ከተወሰነ በኋላ እንዲከፈላቸው የተደረገው ግን አመልካች  የጠየቋቸው ክፍያዎች ሁሉ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ የስራ ውል ከህግ ውጪ ነው የተቋረጠው እየተባለ ውጤቱ በግልፅ ዳኝነት ተጠይቆበት በዝምታ ማለፍ የአሠሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅን አላማ የሚፃረር ነው፡፡ 

ስለዚህም የአመልካች የስራ ውል የተቋረጠው በህገ-ወጥ መንገድ ነው እየተባለ በአመልካች የተጠየቁት ክፍያዎች ውስጥ የካሣ ክፍያን ይኸው ክፍያ ለዘገየበት ጊዜ እና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ጥያቄዎች በዝምታ መታለፋቸውን የስራ ስንብት ክፍያ በአማራጭ መወሰኑ አግባብ አይደለም በማለት ይህ ችሎት የስር ፍ/ቤት ውሳኔዎችን አሻሽሏል፡፡ 

በአጠቃላይ ከዚህ መዝገብ መረዳት እንደሚቻለው የስራ ውል ከህግ ውጪ መቋረጡን በተመለከተ አንድ ፍ/ቤት ውሳኔን ሲሰጥ የኢንዱስትሪውን ሰላም የመጠበቅና የሰራተኛውን የመካስ መብቱን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም አንድ በህገ ወጥ መንገድ ውሉ የተቋረጠበት ሠራተኛ በህጉ መሠረት ሊከፈሉ የሚገቡ ውሳኔዎችን በሙሉ ሊከፈለው ይገባል፡፡ 

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን 

ኢሜይል  ፡-[email protected]

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ… ማግኘት ይችላሉ፡፡

Scroll to Top