የስጦታ ውል የይርጋ ጊዜ ገደብ አለው?

የስጦታ ውል በምን ያህል ጊዜ መፈፀም አለበት በሚለው ጥያቄ ረገድ የተመለከተ ድንጋጌ የለም፡፡ ይሁን እንጂ የስጦታ ውል ድንጋጌዎች በዚህ ረገድ ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ የለም ተብሎ የስጦታ ውል ይፈፀም ጥያቄ በማንኛቸውም ጊዜ ሊቀርብ ይችላል ሊባል አይችልም፡፡ የስጦታ ውልን የሚገዙ ድንጋጌዎች ግልፅ የሆነ ጊዜ ገደብ ባያስቀምጡም ስጦታ ውል እንደመሆኑ መጠን ሊፈፀም የሚገባው በአስር አመት ጊዜ ገደብ መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1676(1) እና 1845 ድንጋጌዎች ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ እንደሚቻል የፌደራል ሰበር ችሎት በመ.ቁ 42691 በሰጠው ውሳኔ ላይ አመልከቷል፡፡

በጉዳዩ መሠረትም በቦሌ ክ/ከ ቀበሌ 15 ክልል ውስጥ የሚገኘውን ቤት ተጠሪ ከሟች ወ/ሮ አለሚቱ በላይነህ በስጦታ የተላለፈላቸው መሆኑን አመልካች ወንድማቸው በመሆኑ በጊዜው ሲቸግራቸው ቤቱን እንዲጠቀሙበት ተጠሪ ፈቅደውላቸው ይዘውት ሲጠቀሙበት ከቆዩ በኋላ ቤቱን እንዲለቁላቸው ሲጠየቁ አመልካች ፍቃደኛ ስላልሆኑ ቤቱን ለቀው እንዲያስረክቡላቸው ጠይቀዋል፡፡

ነገር ግን ተጠሪ የስጦታ ውሉ ሐምሌ 26 ቀን 1972 ዓ.ም ተደርጉልኛል እያሉ ስጦታ አድራጊያቸው በህይወት እያሉ አከራካሪውን ቤት በስጦታ ውሉ መሠረት እንዲፈፀምላቸው ያቀረቡት ጥያቄ የለም፡፡ የስጦታ ውሉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ክሱ እስከተመሠረተበት እስከ ጥር 21 ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በህጉ የተመለከተው የአስር አመት ጊዜ ገደብ አልፏል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ማብራሪያዎች በመስጠት ችሎቱ ተጠሪ ስጦታውን መሠት አድርገው የአቀረቡት የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄ በይርጋ የታገደ ነው ሲል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ከዚህም መረዳት የሚቻለው ምንም እንኳን የስጦታ ውል የይርጋ ጊዜ ገደብ በግልፅ ባይቀመጥም ውል እንደመሆኑ መጠን በአስር አመት ጊዜ ውስጥ በይርጋ እንደሚታገድ ነው፡፡

ኢሜይል ፡-[email protected]

አግባብነትያላቸውተጨማሪህግመረጃዎችከማናቸውምኢትዮጵያዊጠበቃ፣ኢትዮጵያዊታክስጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየቤተሰብጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየወንጀልጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየንብረት/ውርስጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየካሳጠበቃ፣ኢትዮጵያዊፍቺጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየጉዲፈቻ ጠበቃ ማግኘትይችላሉ፡፡

Scroll to Top