የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን የዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 2/2003

የተከበራችሁ አንባቢያን መንግስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን በተመለከተ አዲስ አዋጅ ማውጣቱን ተከትሎ ዝረዝር መመሪያን በማውጣት ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህ መካከልም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን የዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪዎችን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ቁጥር 2/2003 አንዱ ነው፡፡ የዚህን ዝርዝር ከዚህ በታች ያገኙታል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን የዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 2/2003

መግቢያ

የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት በጀታቸውን ለዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪ ሲመድቡ እንዴት ማስላት እንዳለባቸው የሚያሳይ የአፈጻጸም መመሪያ በማውጣት ግልፅነትና ተጠያቂነት በማስፈን ሀብቱን ለተፈለገው አላማ እንዲውል ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ዓመታዊ የበጀት ዕቅዳቸውን፤ የፕሮጀክት ፕሮፖዛላቸውንና የበጀት አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ሲያቀርቡ ሕጉን የተከተለ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል መመሪያ አስፈላጊ በመሆኑ፤

ኤጀንሲው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን የሂሳብ መግለጫና የኦዲት ሪፖርት፤ የዘርፍ አስተዳዳሪዎች ደግሞ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል በሚገመግሙ ወቅት የበጀት ድልድሉና የተፈፀሙ ወጪዎች ለዓላማ ማስፈጸሚያና ለአስተዳደራዊ ስራዎች መመደብ በሚገባው ስሌት አግባብ መሆኑን ለማረጋገጥ፤

ኤጀንሲው የዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪዎችን በተመለከተ ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ የማውጣት  ስልጣን  በደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 በተደነገገው መሰረት የሚከተለው መመሪያ ወጥቷል፡፡

ምዕራፍአንድ

ጠቅላላድንጋጌ

አንቀጽ – አውጪውአካል

የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 621/2001 ለማስፈፀም በወጣው የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 34 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

አንቀጽ – አጭርርዕስ

ይህ መመሪያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን የዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪዎች ለመወሰን የወጣ የአፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 2/2003 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

አንቀጽ – 3 ትርጓሜ

በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሠጥ ካልሆነ በስተቀር፤

  1. አዋጅ ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራትን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣ አዋጅ ቁጥር 621/2001 ነው፡፡
  2. ደንብ ማለት ስለበጐ አድራጐት ድርጅቶች እና ማህበራት ምዝገባና አስተዳደር የወጣ የሚንስትሮች ም/ቤት ደንብ  ቁጥር 168/2001 ነው፡፡
  3. ኤጀንሲ ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ነው፡፡
  4. ቦርድ ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ቦርድ ማለት ነው፡፡
  5. ዋናዳይሬክተር ማለት የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ነው፡፡

6. “አስተዳደራዊወጪ ማለት ለደመወዝ፣ ለአበል፣ ለጥቅማ ጥቅም፣ ለእቃዎችና ለአገልግሎቶች ግዢ፣ ለጉዞ እና ለመስተንግዶ የሚወጡ፣ለበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ አስተዳደራዊ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ወጪ ነው፡፡

7. “ዓላማማስፈጸሚያወጪ” ማለትየበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማኀበሩ የቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት ኀብረተሰቡን ተጠቃሚ ለሚያደርጉ ስራዎች ወይም ተግባራት የሚወጣ ወጪ ነዉ፤

8. “ስብስብ ማለት ለዚህ መመሪያ አፈፃፀም እንዲያግዝ ተቀራራቢ ወይም ተመሣሣይ አላማ ያላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት ወጥ የሆነ የአላማ ማስፈፀሚያ የወጪ አሰላል እንዲከተሉ የሚያስችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት አደራጃጀት ነው፡፡

9. “ጥቅማጥቅም ማለት ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማኀበር ለሠራተኞቹ በጥሬ ገንዘብ ወይም በአይነት የሚሰጥ ክፍያ ወይም አገልግሎት ሆኖ ፕሮቪደንት ፈንድ፣ ቦነስ፣ ካሣ፣ የስራ ስንብት ክፍያ፣እና ዋስትና የመሣሠሉትን ያጠቃልላል፡፡

10. “የሂሳብመግለጫማለት ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማኀበር ወይም የበጎአድራጎት ኮሚቴበበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ ለኤጀንሲው የሚያቀርበው የሀብትና እዳ ሚዛን ትንተና በዓመቱ የሰበሰበውን የገቢ መጠንና ምንጩን እንዲሁም የወጪዎችን ዝርዝር ተቀባይነት ያለው የሂሳብ አሰራርን በመከተል ሠርቶ የሚያቀርበው ሰነድ ነው፡፡

11. “የኦዲትሪፖርትማለት በኦዲተር ተመርምሮ አስተያየት የተሰጠበት የበጐ አድራጐት ድርጅቱን ወይም ማኀበሩን ወይም የበጎ አድራጎት ኮሚቴዉንየሀብትና እዳ ሚዛን ትንተና በዓመቱ የሰበሰበውን የገቢ መጠንና ምንጩን እንዲሁም የወጪዎችን ዝርዝር ተቀባይነት ባለው የሂሳብ አሰራርን በመከተል ሠርቶ የሚያቀርበው ሰነድ ነው፡፡

12. በአዋጅና በማስፈፀሚያ ደንቡ ላይ የተቀመጡት ሌሎች ትርጓሜዎች በዚህ መመሪያ ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

13. በዚህ መመሪያ ዉስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ያካትታል፡፡

አንቀጽ – 4 የተፈጻሚነትወሰን

ይህ መመሪያ:-

. ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች በሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማኀበራት  ወይም የአባላት ጥንቅራቸዉ ከአንድ ክልል በላይ በሆኑ ማኀበራት፤

. በአንድ ክልል ብቻ የሚሰሩ ቢሆንም በዉጭ አገር በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኀበራት፤

. በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኀበራት፤

መ. በአዋጁ አንቀጽ 48 መሰረት በኤጀንሲው ቀርበው የማጽደቅ ውሳኔ የተሰጣቸው የበጎ አድራጎት ኮሚቴዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

አንቀጽ – 5 የመመሪያውዓላማ

የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት በጀታቸውን ለዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪዎች ሲመድቡ ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ ተፈፅሞ ሀብቱ ለተፈለገ የልማት ዓላማ መዋል እንዲችል ለማድረግና አፈፃፀሙም የሕዝቡ የላቀ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ አግባብ መሆኑን ለመከታተልና ለመቆጣጠር ነው፡፡

ምዕራፍሁለት

የበጐአድራጐትድርጅቶችወይምማኀበራትስብስብና (Cluster) የወጪዎችዝርዝር

አንቀጽ – 6 ስብስብ

የበጐ አድራጐት ድርጅቶች  በአዋጁ አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 2 (ሀ-ኘ)፤እና አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 3 በሚፈጥሩት አደረጃጀትና የሚሰማሩባቸውን አላማዎች መሠረት በማድረግ ተመሣሣይና ተቀራራቢነት አላማ ያላቸውን በመለየት ለዓላማ ማስፈፀሚያ በጀት ለማስላት በሚያመች መልኩ ከዚህ በታች በተመለከቱት ስብስቦች  እንዲደራጁ የተደረገ ሲሆን ማኀበራት ግን በይዘታቸዉ የተለያዩ ቢሆኑም ዓላማቸዉ የአባሎቻቸዉን ጥቅም ማስጠበቅ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ስብስብ ሳያስፈልጋቸው  በተለየ ሁኔታ ለብቻቸዉ ይታያሉ፤ ስብስቦቹም፡-

  1. በሴቶችና ህፃናት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤
  2. በኤች.አይቪ.ኤድስ መከላከል እና ጤና ማስፋፋት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤
  3. በግብርና፣ ምግብ ዋስትና፣ህይወት ማዳንና አካባቢ ጥበቃ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤
  4. በትምህርት ማስፋፋት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤
  5. በአካል ጉዳተኞች፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችና አረጋዊያን በመደገፍ ስራ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤
  6. በባህል፣ ቅርስ፣ ወጣቶችና ስፖርት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤
  7. በሰብዓዊና ዴሞክራሲያው መብቶች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤
  8. በግጭት አፈታት፣ የፍትህና የህግ አፈጻጸም ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤
  9. በአቅም ግንባታ፤ምርምርና ጥናት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤
  10. በስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ናቸው::

አንቀጽ – 7 ስብስቦቹንስለማሻሻል

የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማኀበራትበሚፈጥሩት አደረጃጀትና ከሚሰማሩባቸው አላማዎች አንጻር በዚህ መመሪያ አንቀጽ 6 ላይ የተዘረዘሩት ስብስቦች ቢኖሩም ኤጀንሲው አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሊያሻሽለዉ ይችላል

አንቀጽ – 8 የአስተዳደራዊወጪዎችዝርዝር

1.1 በጎአድራጎትድርጅቶች

በአዋጁ አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀጽ 14 የተደነገገው የአስተዳደራዊ ወጪዎች ትርጉም እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ከዚህ በታች የተመለከቱትን ወጪዎች በአስተዳደራዊ ወጪ ስር ሊይዝ ይገባዋል፡፡

ሀ. ለተለያዩ የቢሮ ስራዎች (ለአስተዳደራዊ ስራዎች) ለሚውሉ አገልግሎቶችና እቃዎች የሚፈፀሙ ክፍያዎች፡- አላቂ እቃዎች ግዢ፣ ለቋሚ እቃዎች ግዢ፤ ጥገናና እድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣ለፓርኪንግ የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ለኦዲት አገልግሎት፣ ማስታወቂያ፣ ለባንክ አገልግሎት፣ መብራት፣ ስልክ፣ ፋክስ፣ ውሃ፣ የህትመት ወጪዎች፣ ፖስታ፣ የቢሮ ኪራይ፣ ታክስ፣ ኢንተርኔት፣የወለድ ወጪ (Interest Expense)፤ የአባልነት መዋጮ፤ለተሸከርካሪዎች ግዢ፤ጥገና፤የነዳጅና ዘይት እንዲሁም ለዋስትና የሚደረጉ ወጪዎች፣ የቅጣት ክፍያዎች፣ የማማከር አገልግሎት ክፍያ (Consultancy fee)፣የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ፣ለቅጥር የሚወጡ ወጪዎች፣ክትትልና ቁጥጥር ለማካሄድ የሚወጡ ወጪዎች፣ የተለያዩ ስብሰባዎች ለማካሄድ የሚደረጉ ወጪዎች፤ እቅድና ሪፖርት ዝግጅት፣የምዝገባ ወጪ፤ለተጠቃሚዎች ከሚከፈለው ውሎ አበልና የስልጠና ማቴሪያል ለማዘጋጀት ከሚወጣው ወጪ ውጭ ያለው ማንኛውም የስልጠና  ወጪ እና  ውሎ  አበል ፤ለመስተንግዶና ለጉዞ የሚወጡ ወጪዎች::

ለ. ከሥራው ጋር ወይም ዓላማውን ለማሳካት አገልግሎት ለሚሰጡ የሥራ መሪዎች እና  ለደጋፊ ሰጪሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፣ አበልና ጥቅማ ጥቅም ሆኖ የሚከተሉትን ሠራተኞች ያጠቃልላል፡፡ ማንኛውም የሥራ መሪ፣ ሂሳብ ሹም፤ አስተዳደርና ፋይናንስ፣ ንብረት ክፍል፣የትራንስፖርት ስምርት፣ ገ/ያዥ፣ ኦዲተር፣ ጥበቃ፣ ሹፌር፣ የፕሮግራምና የፕሮጀክት ዳይሬክተር(አስተባባሪ)፤ የሰው ሀብት አስተዳደር፣ ተላላኪ፣ ጽዳት ሠራተኛ፣አትክልኛ፤ ፀኀፊ እና  የመሳሰሉት ሰራተኞች::

ሐ. ማንኛውም የቢሮ ግንባታና ጥገና፤ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ወጪ፤እንዲሁም   የአጥር ግንባታ ወጪ፡፡

1.2 ማህበራት

በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 ከተዘረዘሩት የበጐ አድራጎት ድርጅቶች አስተዳደራዊ ወጭዎች ውስጥ የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚወጣ ወጪ የአዳራሽ ኪራይ፣ሪፖርት ዝግጅት ወጪ፤እንዲሁም ለአጋር ማህበራት ከሚከፈል የአባልነት መዋጮ በስተቀር ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎች ለማኀበራትም ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

1.3 በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) እና (2) የተዘረዘሩት ወጪዎች እንደተጠበቁ ሆነዉ ኤጀንሲዉ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሊያሻሽለዉ ይችላል፡፡

አንቀጽ – 9 የዓላማማስፈፀሚያወጪዎችዝርዝር

የዓላማ ማስፈፀሚያ ወጪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚፈጥሩት አደረጃጀትና የሚሰማሩባቸውን ዓላማዎች መሠረት በማድረግ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 6  ስር በተቀመጠው አግባብ ለየስብስቡ ተለይቶ ከዚህ መመሪያ ጋር በተያያዘው አባሪ 1 እንዲሁም ማኀበራትን በተመለከተ በአባሪ 2ላይ የተዘረዘረ ቢሆንም ከዚህ በታች የተገለጹት የዓላማ ማስፈጸሚያ ወጪዎች ተብለው ይያዛሉ።

ለተጠቃሚዎችየሚደረጉየተለያዩድጋፎች፡የአልባሳት፤ ለተጠቃሚዎች የሚውል የጽህፈት መሣሪያ ግዥ፣የገንዘብ ድጋፍ፤ የምግብ አቅርቦት፣የማምረቻ መሳሪያዎች እና ጥሬ ዕቃ አቅርቦት ግዢ፤ ኬሚካሎች ግዢ፣የመድሐኒት፣የህክምና ወጪዎች ፣ የማምረቻ መሣሪያዎች ድጋፍ፤መኖ አቅርቦት፤ ለእንስሳት ግዥ፤ የተሻለ ቴክኖሎጂ አቅርቦት የሚወጣ ወጪ፣ ለምርቶቻቸው መሸጫ ቦታ ግንባታ  የሚወጣ ወጪ ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች፤

ከዓላማውጋርቀጥታተያያዥለሆኑግንባታዎችየሚወጡድጋፎች፡ለግንባታ የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና የግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውል የውሀ፤የመብራት እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች አቅርቦት፡፡

.ለተጠቃሚዎችግንዛቤማስጨበጫለሚሰሩስራዎችየሚደረግወጪ፡– (ድራማ፣የህትመት ውጤቶች፣ የአየር ሰዓት ክፍያ፣ የሰልጣኞች አበል፣ የስልጠና ማቴሪያል ዝግጅት ወጪ)፤

ከአፈርናውሃጥበቃሥራዎችጋርበቀጥታለሚገናኙተግባራትየሚወጡወጪዎች፡

ፓርኮችንከማልማትናከመጠበቅጋርበቀጥታለሚገናኙተግባራትየሚወጡወጪዎች

. የበጎአድራጎትድርጅቱወይምማህበሩየተቋቋመበትንአላማከማሳካትአንጻር ለተጠቃሚዎች ከሚሰጡ አገልግሎቶች ጋር በቀጥታ ተያያዥ የሆኑ ስራዎች ላይ ለተሰማሩ ሰራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤ ለትምህርት ቤቱ መምህራን፣ በጤና ተቋሙ ለጤና ባለሙያዎች፣ ለግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ ለመጠጥ ውሃ ቁፋሮ ማሽን ኦኘሬተር፣ ለህጻናት ሞግዚቶች ወይም ተንከባካቢዎች እና ለመሳሰሉት፡፡

አንቀጽ – 10 ስለሕብረትወጪዎች

1. የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሕብረቶች በአዋጁ አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 4 መሠረት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሥራዎቻቸውን ለማስተባበር፣ ለመደገፍ እና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለማካሄድ የሚያቋቋሙት ሆነው የገቢ ምንጫቸውም ፡-

ሀ. ከሕህብረቱ አባል ድርጅቶች የሚከፈል ዓመታዊ የአባልነት መዋጮ እና

ለ. ሕብረቶቹ በአባል ድርጅቶቹ ስም ለልማት ከሚያሰባስቡት ሀብት አባል ድርጅቶቹ ለአስተዳደራዊ ወጪ ከሚጠቀሙበት ከ30 ከመቶ ድርሻቸው ላይ ጠቅላላ ጉባዔያቸው በሚወስነው መጠን መሠረት የሚገኝ ገቢ ይሆናል፡፡

2. የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኀበራት ሕብረቶች ፈፃሚዎች ባለመሆናቸው አስተዳደራዊ ወጪ እንጂ የዓላማ ማስፈፀሚያ ወጪ አይኖራቸዉም፣

3 የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እንደተጠበቀ ሆኖ ሕብረቶቹ የሚያሰባስቡት ሀብትና ወጪያቸው ጠቅላላ ጉባኤ በሚያጸድቀው ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

አንቀጽ – 11 አስፈላጊውንየሰውሀይል፣የደመወዝእናየማቴርያልመጠንስለመኖር

ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር ሰራተኛ ሲቀጥር የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ  እያከናወነ ካለው ስራ አንጻር የግድ የሚያስፈልጉ ሰራተኞችንና  ማቴሪያል የተመጣጠነ የሰው ሀይልና ሎጂስቲካዊ አቅርቦት ብቻ መሆን አለበት።

በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ የተገለጸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛዉም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር ለሚቀጥረዉ ሰራተኛ የሚከፍለው የደመወዝ መጠን (scale) ከአገሪቷ ኢኮኖሚ ጋር ተመጣጣኝና ያልተጋነነ መሆን ይኖርበታል፡፡

. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ ስር የተጠቀሰው ቢኖርም ይህንን  መመሪያ በማክበርና እንዲከበር የተንቀሳቀሱ ወገኖችን ለመጉዳት የሚንቀሳቀስ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ወይም የስራ መሪ መኖሩ ከተረጋገጠ ኤጀንሲው በበጎ አድራጎት ድርጅቱ ወይም ማኀበሩ ወይም የስራ መሪ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ እንዲከብድ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ክፍልሦስት

ልዩልዩድንጋጌዎች

አንቀጽ – 12 የህግተጠያቂነት

. የዚህን መመሪያ ድንጋጌዎች የጣሰ ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር በአዋጁ አንቀጽ 102 በተደነገጉት ቅጣቶች መቀጣቱ እንዳለ ሆኖ ኤጀንሲዉ እንደ አስፈላጊነቱ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከስረዛ መሄድ የሚችል እርምጃ ይወስዳል፡፡

. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ከጠቅላላ ዓመታዊ በጀቱ ከ80 በመቶ በላይ ለዓላማው ማስፈጸሚያ ለሚያውል ወይም የላቀ የስራ አፈጻጸም ላሳየ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር ኤጀንሲው የተለያዩ ማበረታቻዎችን ሊያደርግ ይችላል፡፡

አንቀጽ – 13 ተፈፃሚነትስለማይኖራቸውመመሪያዎች

ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ ወይም ባህላዊ አሰራር   ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡

አንቀጽ -14 መመሪያዎችስለሚሻሻልበትሁኔታ

ኤጀንሲው ይህንን መመሪያ ተግባራዊ ሲያደርግ የሚከሰቱ ክፍተቶችን ለመሙላት አዋጁንና ደንቡን የሚጠቀም ሲሆን በሂደት ከሚያገኛቸው ልምዶች በማንኛውም ጊዜ ሊያሻሽለው ይችላል፡፡

አንቀጽ– 15 መመሪያውየሚጸናበትጊዜ

ይህ መመሪያ በቦርዱ ፀድቆ ከወጣበት ከሐምሌ 9 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

አዲስአበባሐምሌ 2003 .

ዓሊሲራጅ

የበጎአድራጎትድርጅቶችናማህበራትኤጀንሲ

ዋናዳይሬክተር

አባሪ 1

ለበጎአድራጎትድርጅትስብስቦችየዓላማማስፈጸሚያወጪዎችዝርዝር

በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5 ለተዘረዘሩት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ስብስቦች የዓላማ ማስፈፀሚያ ወጪዎች የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡

7.1 በህፃናትናሴቶችዙሪያየሚንቀሳቀሱየበጐአድራጐትድርጅቶች

ሀ. የትምህርት አገልግሎትን ለማስፋፋት የሚወጡ ወጪዎች፡- ለትምህርት ቤት ወይም ለስልጠና ማዕከላት ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችና ሌሎች ቋሚ ዕቃዎች ግዥ፣ለህጻናቱ ወይም ለሴቶቹ ዶርሚተሪና መጸዳጃ  ቤት ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና  ዕድሳት ወጪዎ፡፡

ለ. ጤና  አገልግሎት ማስፋፋትን መሰረት ያደረገ ወጪዎች፡-የጤና ተቋማን  ለመገንባትና ዕድሳት ለማካሄድ  የሚደረጉ የጥሬ እቃዎችም ሆነ የግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣ስነ-ተዋልዶና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ወጪዎች፣ ለህፃናት ንጽህና አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ግዥ፣የህክምና መሣሪያዎች፣ አገልግሎቶች እና መድሃኒት ግዢ፡፡

ሐ. ለህፃናቱ ወይም ለሴቶች የሚደረጉ የተለያዩ ድጋፎች፣ (የአልባሳት፤ለተጠቃሚዎች የሚውል የጽህፈት መሣሪያ ግዥ፤ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣የገንዘብ ድጋፍ፤የምግብ አቅርቦት፣የማምረቻ መሳሪያዎች እና ጥሬ ዕቃ አቅርቦት ግዢ፤ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች)

መ. ለተጠቃሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ለሚሰሩ ስራዎች የሚደረግ ወጪ።(ድራማ፣የህትመት ዉጤቶች፤የአየር ሰዓት ክፍያ)፤

ሠ. በኤች.አይ.ቪ.ኤድስ መከላከል በጤና አጠባበቅ ዙሪያ እንዲሁም ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቀረት ለተጠቃሚዎች በሚደረጉ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች የሚወጣ ወጪ (ለተጠቃሚዎች የሚከፈል የውሎ አበልና የስልጠና ማቴሪያሎች ግዥ)፡፡

ረ. ለሞግዚቶች፣ በጤና ተቋሙ ለጤና ባለሙዎች አንዲሁም ህጻናቱን ለሚያስተምሩ  መምህራን የሚከፈል ደመወዝ፡፡

7.2 በጤናናኤች.አይ..ኤድስዙሪያለሚንቀሳቀሱ

ሀ. ለቫይረሱ ተጠቂዎችም ሆነ ተጋላጭ ወገኖች የሚደረግ ማንኛውም የምክርና የደም ምርመራ አገልግሎት ወጪ፣ የኮንዶም ሥርጭት፣ የመድኃኒት ግዥና አቅርቦት፣ የምግብና የአልባሳት ወጪ፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ እራሳቸውን እንዲችሉ ታስቦ የሚሰጥ የሙያ ሥልጠና፣ የማምረቻ መሣሪያዎች ድጋፍ፡፡

ለ.  ጤና አገልግሎት ማስፋፋትን መሰረት ያደረገ ወጪዎች፡-የጤና ተቋማን  ለመገንባትና ዕድሳት ለማካሄድ  የሚደረጉ የጥሬ እቃዎችም ሆነ የግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣ስነ-ተዋልዶና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ወጪዎች፣ ለህፃናት ንጽህና አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ግዥ፣የህክምና መሣሪያዎች፣ አገልግሎቶች እና መድሃኒት ግዢ፡፡

ሐ. በኤች.አይ.ቪ.ኤድስ መከላከልም ሆነ በጤና አጠባበቅ ዙሪያ ያተኮሩ ለተጠቃሚዎች ለሚሰጡ  የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች (ለተጠቃሚዎች የሚከፈል  ውሎ አበል፣ የስልጠና ማቴሪያሎች ግዥ)፡፡

መ. ለወባና ውሀ ወለድ እንዲሁም ሌሎች ተላላፊ እና ተዛማች በሽታዎችን ለመከላከል ለሚሠሩ የአቅርቦትና የመከላከል ሥራዎችና ለክትባት የተደረገ ወጪ፡፡

ሠ. ለግንዛቤ ማስጨበጫ ለሚሰሩት ስራዎች የሚደረግ ወጪ።-(ድራማ፣የህትመት ዉጤቶች፤የአየር ሰዓት ክፍያ)፤

ረ. ለሞግዚቶች እና ፣ለጤና ባለሙያዎች  የሚከፈል ደመወዝ፡፡

7.3 ብርና፣ምግብዋስትና፣ህይወትማዳንናአካባቢጥበቃዙሪያየሚንቀሳቀሱ

ሀ. ምርትን ለማሳደግና ለተሻሻለ ቴክኖሎጂ አቅርቦት  የሚደረግ ወጪ።-ምርጥ ዘር ብዜትና ስርጭት፣ ፀረ-ተባይ፣ ፀረ አረም፣ የግብርና መሣሪያዎች፣ ሀይል ቆጣቢ ምድጃ፣ ሶላርና ለባዮጋዝ ግንባታ ወጪ፣ ማዳበሪያ፣ ፕላስቲክ ባግ ግዢ፣ለመሰረተ ልማት ግንባታ የሚወጡ ወጪዎችና ለገጠር ብድር አገልግሎቶች የሚሰጥ የገንዘብና ቁሳዊ  ድጋፍ  እንዲሁም የመጋዝን ኪራይ ወይም ግንባታ፡፡

ለ. ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የሚወጡ ወጪዎች፡ ችግኝ ማፍላት፣ ስርጭትና  ተከል፣ እርከን ሥራ፣ ዎተር ሼድ ማኔጅመንት፣ ለአነስተኛ መስኖ ግንባታና ጥገና የሚደረግ ወጪ፡፡

ሐ. ለአርሶ አደሩም ሆነ ለአርብቶ አደሩ በገቢ ማስገኛ ሥራዎች፣ በአካባቢ ጥበቃ፡በምግብ ዋስትናና በግብርና ልማት ዙሪያ ለሚሠጡ ስልጠናዎች የሚወጣ ወጪ፤ (ለተጠቃሚዎች የሚከፈል የውሎ  አበል፣ የስልጠና ማቴሪያሎች ወጪ፣ የስልጠና ማእከላት ግንባታ ወጪ) እና ሌሎች ድጋፎች፡፡

መ. የአካባቢን ብክለት ለመቀነስ የሚከናወኑ የምርምር ዉጤቶችን ተግባር ላይ ለማዋል  የሚወጣ ወጪ፡፡

ሠ. የእንስሳትን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅ የሚደረግ ግንባታ፣ የህክምና መድኃኒት አቅርቦትና አገልግሎት፣ መኖ አቅርቦት፤ ለእንስሳት ግዥ፣ የዱር እንሰሳትን ደህንነት፣ ፓርኮችን ለማልማትና ለመጠበቅ የሚረዱ ቁሳዊና የገንዘብ ወጪ፡፡

ረ. ህይወትን ለማዳን የሚወጣ ወጪ፡- የድንኳን ግዢ፣ መጠለያ፣ የምግብ አቅርቦት፣ህይወትን ለማዳን የሚያስፈልጉ ቦቲዎችና ጀልባዎች፣ ነዳጅና መኪና ኪራይ፣መድሀኒት ግዥና አቅርቦት፡፡

ሰ. ደመወዝ ለግብርና ኤክስቴንሽን  ባለሙያዎች  የሚከፈል ደመወዝ፡፡

7.4 በትምህርትዙሪያየሚንቀሳቀሱ

ሀ. የትምህርት አገልግሎትን ለማስፋፋት የሚወጡ ወጪዎች፡- ለትምህርት ቤት ወይም ለስልጠና ማዕከላት ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና  ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፣የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችና ሌሎች ቋሚ ዕቃዎች ግዥ፣ለህጻናቱ ወይም ለሴቶቹ ዶርሚተሪና መጸዳጃ ቤት  ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና  ዕድሳት ወጪዎች፡፡

ለ. ለተማሪዎች የሚደረጉ የተለያዩ ድጋፎች፤(የአልባሳት፤ለተጠቃሚዎች የሚውል የጽህፈት መሣሪያ ግዥ፤የህክምና አገልግሎት ወጪ፣የገንዘብ ድጋፍ፤የምግብ አቅርቦት፣ የሙያና የቴክኒክ ስልጠናዎችና ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች)፤

ሐ. ለት/ቤቱ  መምህራን የሚከፈል ደመወዝ፤

7.5 አካልጉዳተኞች፣ጎዳናተዳዳሪዎችናአረጋዊያንዙሪያየሚንቀሳቀሱ

ሀ. እንደየአግባብነቱ ለአካል ጉዳተኞችም ሆነ ለአረጋዊያን   የሚደረጉ የተለያዩ ድጋፎች፡-የተለያዩ አጋዥ መሳሪያዎች ድጋፍ( ብሬይል፣ ዊልቸር፣ ትራይ ሳይክል፣ መነጽር እና  የመሳሰሉት)፤ የአልባሳት፣ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ ፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ የምግብና መጠለያ፣ የህክምና ወጪዎች ፣ የማምረቻ መሣሪያዎች ድጋፍ፤ የጥሬ ዕቃዎች ግዥ፣ ለምርቶቻቸው መሸጫ ቦታ ግንባታ  የሚወጣ ወጪ፡፡

ለ. ለመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ግንባታ  የሚወጣ ወጪ (ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ለመጸዳጃ ቤት፤ለመኖሪያ ቤት፤ ለመብራት አቅርቦት፡፡

ሐ. የአካል ጉዳተኞችን፤አረጋዊያንና ጎዳና ተዳዳሪዎችን በተመለከተ ለሚታተሙ የህትመት ውጤቶች የሚደረጉ ወጪዎችና ለሚዲያ አስተምህሮት የሚወጡ ወጪዎች፤

መ. እራሳቸውን እንዲችሉ የሚደረግ ሙያዊ ስልጠና( ለተጠቃሚዎች የሚከፈል አበል፤የስልጠና ማቴሪያል ዝግጅት ወጪ)፡፡

ሠ. ወይም ለሞግዚቶች የሚከፈል ደመወዝ፡፡

7.6 ለጥበብ፣ባህል፣ቅርስወጣቶችናስፖርትዙሪያየሚሰሩ

ሀ. ለስፖርተኞችና ለዘርፉ ተብሎ የሚካሄድ የስፖርት  ትጥቆችንና የስፖርት ቁሳቁሶች ግዥ፣ የገንዘብ ድጋፍና ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች፡፡

ለ. በውድድርም ሆነ በልምምድ  ለስፖርተኞች የህክምና ወጪ፣ ለአሸናፊዎች የሚሰጥ የሽልማት ወጪ፡፡

ሐ. የስፖርትና የወጣት ማዕከላት፣ የቤተ መጽሐፍት ግንባታና ጥገና፤የውስጥ ቁሳቁስ ለማደራጀት የሚወጣ ወጪ፣ ስነ-ጥበብና ኪነ-ጥበብ እንዲስፋፉ የተደረገ የቁሳቁስ ድጋፍ

መ. ስራ አጥ ወጣቶችና ሴቶችን  የሙያ ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት ለመገንባትና የውስጥ ቁሳቁስ ለማደራጀት የሚደረግ ወጪ፣የማምረቻና መሸጫ ቦታ ዝግጅት ወጪ፣የገንዘብና ሌሎች ቁሳዊ  ድጋፎች፣የስልጠና ማቴሪያል ዝግጅት ግብዓት የሚወጣ ወጪ፤

ሠ. ቅርሶችና አገር በቀል ባህሎች  አንዲጠበቁ ለማድረግ የሚካሄድ የሙዚየም ግንባታ፤ ተፈላጊ ቅርሶች መሠብሰብ፣እና ባህልና ቅርስን፣ ቱሪዝም እንዲስፋፋና መዳረሻዎችን የማስተዋወቅ ሥራ ወጪ፡-

ረ. የስፖርተኞች፣ የስፖርት አሰልጣኞች፤ ለስፖርተኞች ወጌሻዎችና ሀኪሞች የሚከፈል ደመወዝ፤

7.7 ሰብዓዊናዴሞክራሲያዊመብቶችዙሪያየሚንቀሳቀሱ

ሀ. በሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ በጐጂ ባህል ቅነሳ፣ በሴቶችና ህፃናት መብት፣ ሕገ መንግሥት፣ ምርጫንና መልካም አስተዳደርን በሚመለከት ለሚሰጥ ስልጠና የሚወጣ ወጪ (ለተጠቃሚዎች የሚከፈል አበል፣ ለስልጠና ማቴሪያሎች ዝግጅት)፤

ለ.  ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በሚመለከት የሚወጣ የህትመቶች ወጪ፤

ሐ.  ሰብአዊ መብት ጥሰቶችን (ተጐጂዎችን) ለመርዳት የሚወጣ የቁሳቁስ ወጪ፤

መ. ምርጫን ለመከታተልና ለመታዘብ የሚወጣ ወጪ(የታዛቢዎች አበል፣ትራንስፖርት ወጪ፣ ለስራው አጋዥ የሚሆን የስልጠናና ማቴሪያሎች ዝግጅት የሚወጣ ወጪ)፣

ሠ. የሚዲያ አየር ጊዜ ክፍያ::

7.8 በግጭትአፈታትናየሕግአፈጻጸምአገልግሎትዙሪያየሚንቀሳቀሱ

ሀ. የግጭት አፈታትን በተመለከተ ለተጠቃሚው የሚሰጥ ስልጠና የሚወጣ ወጪ (የስልጠና ማቴሪያሎች  ዝግጅት፣ የሰልጣየኞች ውሎ አበል)፤

ለ. ማህበረሰብ አቀፍ (community based) ለሆኑ እንደ እድርና የሀገር ሸማግሌዎች ለተለያዩ አደረጃጀት በግጭት አፈታትና ዕርቅ ዙሪያ የሚደረጉ ቁሳዊና የገንዘብ ድጋፍ፣ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች፣እና ባህላዊ የግጭት አፈታትን ለማበረታታት የሚወጣ ወጪ፤

ሐ. በህግ አፈጻጸም ዙሪያ ለተጠቃሚዎች  የሚሰጡ  ሥልጠናዎች ወጪ( ለተጠቃሚዎች   አበል፣ የስልጠና ማቴሪያሎች ዝግጅት፡፡

7.9. በአቅምግንባታ፤ምርምርናጥናትዙሪያየሚንቀሳቀሱየበጎአድራጎትድርጅቶች

ሀ. ለተጠቃሚዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና (ለተጠቃሚዎች የሚከፈል አበል፣ ለስልጠና ማኑዋሎች ዝግጅት የተደረገ ወጪ፤

ለ. ለተጠቃሚዎች የሚሰጥ ማንኛዉም ቁሳዊና የገንዘብ ድጋፎች ያካትታል፤

ሐ. በምርምር ላይ የተሰማራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከሆነ የምርምር ዉጤቶች ለሆኑ  ተግባራት የሚወጣ ወጪ፤

7.10. በስደተኞችናከስደትተመላሾችዙሪያየሚንቀሳቀሱ

  1. ስደተኞችን ለማቋቋም የሚደረጉ የተለያዩ ድጋፎች፡- የምግብ፣የገንዘብና ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች፣ የአልባሳት፣ የመኖሪያ ካምኘ ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች ለድንኳን ግዥዎች የሚወጡ ወጪዎች፤የግንባታና የጥገና ወጪ፤
  2. ለትምህርት እና ለጤና ተቋማት ግንባታ ለሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችና ግንባታ መሳሪያዎች ግዢና ለዕድሳት የሚደረጉ ወጪዎች፤
  3. የተለያዩ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት ለሚደረጉ ግንባታዎች የሚወጣ ወጪ፡-(ለመንገድ ግንባታ፣ የመጸዳጃ ቤት  ግንባታ፣የወፍጮ ቤት ግንባታ፣ የመብራት አቀርቦት፣ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ማከማቻና ማሰራጫ፣ ለምንጭ ማጐልበት)፤
  4. የትምህርት ቁሳቁሶች ግዢ፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና ኬሚካሎች ግዢ፣የመድሐኒት፣ የህክምና አገልግሎት ግዥ፤

አባሪ 2

ማህበራትንበሚመለከትአላማማስፈፀሚያወጪዎች

ማህበራት በአዋጁ አንቀጽ 56(2) እና አንቅጽ 57(7) መሰረት በይዘታቸው፣በባህሪያቸውና በዓላማቸው የአባላቱን ጥቅም ከማስከበር ጋር የተያያዘ በመሆኑ በስብስብ መከፋፈል ሳያስፈልግ ለሁሉም ማህበራት የሚከተሉት ወጪዎች ዓላማ ማስፈፀሚያ ተብለው ይወሰዳሉ፡፡

  1. የአባላቱን አቅም ለመገንባት ለሚሰጡ ሙያዊ ስልጠናዎች የሚወጣ ወጪ (ለስልጠና ለሚያገለግሉ ማቴሪያሎች  ዝግጅት፣ለሰልጣኞች  የሚከፈል የውሎ አበል)፤
  2. ለአባላቱ የሚደረጉ ድጋፎች (የገንዘብ፣ ህክምና፣ ትምህርት፣ ምግብና መጠለያ እንዲሆም ሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች)፣
  3. ማህበሩን በተመለከተ ለሚታተሙ የህትመት ውጤቶች የሚከፈል ክፍያ፤
  4. በምርጫ ዙሪያ ምርጫን ለመታዘብ የሚወጣ ወጪ፡- (ለኢትዮጵያዊያን ማህበራት ብቻ)
  5. ማኀበሩ ምርት ወይም አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የጥሬ ዕቃዎች ግዥ ወጪ፣
  6. ለተለያዩ አጋር ማኀበራት የሚከፈል የአባልነት መዋጮ፤
  7. የማኀበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚወጣ ወጪ እና የአዳራሽ ወጪ፤

አባሪ 3

ህዝባዊመዋጮለሚሰበስቡየበጎአድራጎትድርጅቶችወይምማህበራትየአላማማስፈጸሚያወጪዎች

ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ለሚያካሂደው ህዝባዊ መዋጮ የመሰብሰብ ስራ ከሚኖሩት ወጪዎች የሚከተሉት ብቻ የዓላማ ማስፈጸሚያ ወጪ ተብለዉ ይያዛሉ::

  1. ገቢዉን ለማሰባሰብ የሚሆን ምርትን ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎች ግዢ፡፡
  2. ህዝባዊ መዋጮዉን ለማሰባሰብ የሚደረጉ የማስታወቂያ ክፍያ፡፡
  3. ህዝባዊ መዋጮዉን ለማሰባሰብ የሚያገለግል የአዳራሽ ወይም የቦታ ኪራይ ክፍያ፡፡
  4. ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለደንበኞች ለማቅረብ የሚከፈል የትራንስፖርት ወጪ፡፡

አባሪ 4

ግዴታዎች

የበጎአድራጎትድርጅትወይምማህበራትግዴታዎች

  1. ማንኛውም በጎ አድራጐት ድርጅት ወይም ማኀበር  በዚህ መመሪያ በአንቀጽ 5 ከተገለፁት ስብስቦች አንድና ከአንድ በላይ በሆነ ስብስቦች ላይ ተመስርቶ የሚሰራ ከሆነ፤ ከተመሰረተበት ዓላማ አግባብነት ካላቸው በመለየት አግባብነት ያላቸዉን ስብስቦች ስር የተገለጹትን ዓላማ ማስፈጸሚያ ወጪዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት  ከዚህ መመሪያ ጋር ተያይዞ ካለው አባሪ 1 ስር በተቀመጠው ዝርዝር መሠረት  በበጀት ዓመቱ ያቀደውን ስራና ለእቅዱ ማስፈጸሚያ የመደበውን ወጪ ከጠቅላላው ወጪው ከ70 በመቶ የማያንሰውን ለዓላማ ለማስፈፀሚያ እና ከ30 በመቶ የማይበልጠውን ለአስተዳደራዊ ሥራ መመደቡን በመዘርዘር በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ 3ዐ ቀናት ውስጥ ለኤጀንሲው ማቅረብ ይጠበቅበታል፣
  2. ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር ለኤጀንሲው ባቀረበው ዕቅድ ላይ ዓላማ ማስፈፀሚያና አስተዳደራዊ ወጪውን በተመለከተ ማስተካከያ እንዲያደርግ ኤጀንሲው በጽሑፍ ሲያዘዉ ትዕዛዙ በደረሰው 15 ቀናት ውስጥ ማስተካከያውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  3. ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር በአመቱ መጨረሻ ለኤጀንሲው  የሂሳብ መግለጫና የኦዲት ሪፖርት  ሲያቀርብ ከጠቅላላ ዓመታዊ በጀቱ 70 ከመቶ የማያንሰውን ለአላማ ማስፈፀሚያ ማዋሉ እንዲሁም ከወጪው 30 ከመቶ የማይበልጠውን  አስተዳደራዊ ወጪ ማዋሉ የሚሰላዉ እያንዳንዱን ፕሮጄክት አፈጻጸም በተናጥል ሳይሆን በሁሉም ኘሮጀክቶች ካዋለዉ የበጀት አፈጻጸም አንጻር ነዉ።
  4. ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር የተለያዩ እርከን ካላቸው የመንግስት አካላት፤ወይም ከዘርፍ አስተዳዳሪዎች በመስማማት በአንድ አካባቢ ወይም ክልል ተሰማርቶ የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ለማገልገል ሲንቀሳቀስ ለስራው የመደበው በጀት ለተጠቀሱት አካላት ግልጽ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
  5. ማንኛውም የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር የሂሳብ ሰራተኛ ወይም የውስጥ ኦዲተር ወይም የውጭ ኦዲተር በአዋጁ አንቀጽ 79 እና 80 አንዲሁም በደንቡ አንቀጽ 21 አና 22 የተቀመጡ ድንጋጌዎችን አክብሮ አመታዊ የስራና የኦዲት አፈፃፀም ሪፖርቱን ማዘጋጀት ይጠበቅበታል፤
  6. ማንኛውም ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማኀበራት የገንዘብ ወይም የዓይነት ድጋፍ በማድረግ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ህብረት ወይም ማህበር ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት የገንዘብ ወይም የአይነት ድጋፍ ሲያደርግ በቅድሚያ የገንዘብ ወይም የዓይነት ድጋፍ የሚደረግለት ድርጅት ያገኘው የድጋፍ ገንዘብ ሊያውለው በፈለገው ኘሮግራም ወይም ኘሮጀክት ላይ ከ30% ያልበለጠውን ለአስተዳደራዊ ወጪ ከ70% ያላነሰዉን አላማ ማስፈፀሚያ ወጪ ለማዋል ስምምነት ላይ መድረሱንና ማዋሉን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፡፡
  7. ማንኛውም የገንዘብ ወይም የዓይነት ድጋፍ የሚያደርግ የውጭ ወይም የኢትዮጵያ ነዋሪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ለኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ከ10 ከመቶ በላይ በገንዘብም ሆነ በዓይነት ድጋፍ ሊሰጥ አይችልም፡፡
  8. ከላይ በንዑስ አንቀጽ 7 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ለኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር 10 በመቶ የሚሆን በገንዘብ ወይም በአይነት ድጋፍ ማድረግ የሚችለው ከሌላ ተመሳሳይ የውጭ ምንጭ ድጋፍ አለማግኘቱን በማረጋገጥ ይሆናል፡
  9. ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ኤጀንሲው ተጨማሪ መረጃ እንዲቀርብባቸው የሚፈለጉ ጉዳዮች ወይም ተጨማሪ ማጣራት  በማስፈለጉ ለሚደረግ ምርመራ የበጐ አድራጐት ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ወይም የስራ መሪ ወይም ሰራተኛ መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

የኤጀንሲውግዴታዎች

  1. ማንኛውም የኤጀንሲው  የምዝገባ ፤የክትትልና ድጋፍ ወይም ኦፊሰር በየዓመቱ የሚቀርበውን የበጎ አድራጐት ድርጅት ወይም ማኅበር አመታዊ የበጀት  ዕቅድ፣የሂሰብ መግለጫ ወይም  የሂሳብ ምርመራ ሪፖርት ሲገመግም ይህን መመሪያ መሰረት የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
  2. ማንኛውም የኤጀንሲው የምዝገባ፣ የክትትልና ድጋፍ ወይም ኦፈሰር የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት በበጀት አመቱ መጀመሪያ የሚያቀርቡትን የስራ እቅዶቻቸውን ሲያቀርቡ  ለአስተዳደራዊ ወጪ የተመደበዉ ከ30 በመቶ ያልበለጥ  ለአላማ ማስፈፀሚያ የተመደበዉ ከ70 በመቶ ያላነሰ መሆኑን በመመርመር ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡
  3. በተራ ቁጥር 2 በተገለጸዉ መሰረት በአቀረቡት ዓመታዊ ዕቅድ  የአላማ ማስፈፀሚያና የአስተዳደራዊ ወጪያቸውን በህጉ መሰረት  አሟልተው ያላቀረቡ ድርጅቶች አሟልተው እንዲያቀርቡ የማስተካከያ አስተያየት በጽሑፍ አዘጋጅቶ በመስጠት ለበጐ አድራጐት ድርጅቶች ወይም ማኀበራቱ ማሳወቅ አለበት፡፡
  4. ኤጀንሲው ተጨማሪ መረጃ ማቅረብ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ  የሚመለከተዉን  የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማኀበር እንደአስፈላጊነቱ የጽሑፍ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጊዜ ወስኖ ያሳውቃል፡፡
  5. ኤጀንሲው ተጨማሪ ምርመራው እንዲካሄድ ሲወስን ምርመራው በኤጀንሲው ሙያተኞች ወይም ኤጀንሲው ኦዲተር መድቦ እንዲመረመር ሊያደርግ ይችላል፡፡
  6. የኤጀንሲው ሙያተኞች ወይም በኤጀንሲው የሚመደቡ ኦዲተሮች በማንኛውም ጊዜ የድርጅቱን ወይም ማህበሩን የስራ አፈፃፀም፣ የሂሳብ መግለጫና የኦዲት ሪፖርት ሲመረምሩና የማጣራት ስራ ሲያከናውኑ ሙያው በሚጠይቀው ስነ ምግባር ስራቸውን ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. በንዑስ አንቀጽ 6 የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ ከሙያዊ ስነ ምግባር  ውጭ በሆነ መንገድ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማኀበራት ሕገ ወጥ ጥቅም በመፈለግ ወይም በመቀበል ኃላፊነቱን በማይወጣ የኤጀንሲው  ሠራተኛ ላይ ኤጀንሲው እንደ ጥፋቱ ደረጃ ቅጣት ይጥላል፡፡

የተለያዩአካላትግዴታዎች

መመሪያውንበመተግበርሂደት፡

  1. በአዋጁ አንቀጽ 67 ንዑስ አንቀጽ (2) እና (3) በተደነገገው መሠረት የዘርፍ አስተዳዳሪዎች የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማኅበራትን ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን ሲገመግሙ፣ ስምምነት ሲፈራረሙ እና አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ሲቆጣጠሩ ለዓላማ ማስፈፀሚያ የተመደበው በጀትና አፈጻጸመሙ 70 ከመቶ ያላነሰ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰውን መሰረት
Scroll to Top