የብድርን እጥፍ ለማስከፈል ውል መዋዋል ይቻላል ?

ሁለቱ ሰዎች በሚያዋውሉት የብድር ውል ላይ ተበዳሪው ወገን በተጠቀሰው ጊዜ ብድሩን ካልከፈለ የብድሩን ገንዘብ እጥፍ አድርገው እንዲከፍል የተቀመጠ እንደሆነ በውሉ መሰረት ተበዳሪው ወገን እጥፍ እንዲከፍል ይገደዳል ማለት ነው?

ገዳዩ የተጀመረው በምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ስሆን የክሱም ምክንያት በከሳሽና በተከሳሽ መሃከል የተደረገ የብድር ውል ላይ ተከሳሽ 11,75ዐ.00 (አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) ተበድረው በተባለው ግዜ ካልመለሱ ገንዘቡን በእጥፍ አድርገው እንዲከፍሉ እንዲወሰንላቸው የሚል ነው፡፡ ተከሳሽም በመልሳቸው መክፈል ያለባቸው የተበደሩትን ገንዘብ ልክ እንጂ በእጥፍ መሆን እንደሌለበት ገልፀው ተከራክረዋል፡፡

ይግባኝ የተባለው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤትና የኦሮሚያ የሰበር ሰሚ ችሎትም በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 337 መሠረት ይግባኙን ሰርዘውታል፡፡

ይግባኝ የተባለለትም የሰበር ችሎትም ተዋዋዬች በወለድ የሚከፈለወን ገንዘብ በአመት በመቶ ከአስራ ሁለት በላይ ሲሆን እንደሚችልና ከዚህ በላይ እንዲከፈለ የተደረገ ውል ቢኖር እንኳን ተበዳሪው በመቶ ዘጠኝ ብቻ በአመት መክፈል እንዳለበት በህጉ ተደንግጓል፡፡

በተያዘው ጉዳሥም የብድርን ገንዘብ ከመሸኛው እጥፍ አድርጐ ለመክፈል መዋዋል ሕጉ የሚከላከል ሲሆን፡፡ ከሳሽም ገንዘቡ እጥፍ ተደርጐ ይከፈለኝ ነው ያሉት እንጂ ክፍያው ስለዘገየ በወለድ ይከፈለኝ የሚልን ጥያቄ ሳያነሱ ፍ/ቤት እጥፍ የተባለውን ወለድ በማድረግ 23,500.00/ ሃያ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ እንዲከፍል ማዘዙ አግባብ አይደለም፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትን ማብራሪያዎች በመስጠት ችሎት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በማሻሻል ብድሩን እና የውሉ ጊዜ ካለፈበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ 9% ወለድ እንዲከፍሉ በማለት ውሳኔን አስተላልፏል፡፡

ስለዚህም የብድር ውል የሚዋዋሉ ወገኖች ብድሩ ካልተከፈለ የገንዘቡ እጥፍ እንዲከፈል የማያደርጉት ስምምነት በህግ ተቀባይነት እንደሌለው ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡

ተጨማሪ ጥያቄ አስተያየት ቢኖርዎት ያነጋግሩን ይጠይቁን

ኢሜይል  ፡-[email protected]

አግባብነትያላቸውተጨማሪህግመረጃዎችከማናቸውምኢትዮጵያዊጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየንብረትጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየካሳጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊየዉልጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየንብረትጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየካሳጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፍቺ ጠበቃማግኘትይችላሉ፡፡

Scroll to Top