የጉዲፈቻ ስምምነት የህፃናትን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ሊፈርስ ይችላል?

አንድ ሰዉ ድርጅት አንድን ልጅ በህጋዊ መንገድ በጉዲፈቻ ከወሰደ በኋላ ጉዲፈቻ ስለተደረገው ልጅ የጤንነት ሁኔታ ተመልክቶ ጉዲፈቻው እንዲሰረዝለት ሊጠይቅ ይችላል?

ይህንን አስመልክቶ  የሰበር ሰሚ ችሎት በሚያዚያ 22 ቀን 2002 ዓ.ም ውሳኔን ሰጥቷል፡፡ አመልካቾች ባቀረቡት አቤቱታ በጉዲፈቻ የተወሰደው ልጅ ከውሳኔ በኋላ ሲመረመር የአእምሮ እድገት ዝግመት ያለበት መሆኑ ስለተረጋገጠ የጉዲፈቻ አድራጊዎች በዚህ ምክንያት ልጁን ሊቀበሉ ስላልቻሉ ውሳኔው ይሰረዝልን ሲሉ መጠየቃቸውን ያሳያል፡፡

ይህንን ጉዳይ የተመለከቱት የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤትና የከፍተኛ ፍ/ቤቶችም የቀረበው ምክንያት ውሉን ለማፍረስ የሚያስችል አለመሆኑን ገልፀው ጥያቄውን ውድቅ አድርገውታል ጉዳዩን የተመለከተው የሰበር ችሎት በህገመንግስቱ አንቀፅ 36(1) ስር ከተደነገገው የህፃናትን ጥቅም ማስጠበቅ (Best Interest Of The Child) መርህ አኳያ ተገቢነቱን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ አድርጓል፡፡

በመርህ ደረጃ የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 195(1) በመርህ ደረጃ የጉዲፈቻ ውል ሊፈርስ እንደማይችል ያስቀምጥና በንኡስ ቁጥር 2 ስር ደግሞ ውሉ ሊፈርስ የሚችልባቸውን ልዩ ሁኔታዎች ይደነግጋል፡፡ ከነዚህም በተለይም “በማንኛውም ሌላ መንገድ የልጁን ህይወት የወዲፊት ሕይወት ክፋኛ በሚጐዳው አኳኋን የያዘው” የሚለው ትርጉም እንደማያስፈልገው እንደሆነ ገልጿል፡፡ ይህንንም በማስመልከት ህገመንግስትም ሆነ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች ህፃናትን የሚመለከት ጉዳዮች ለህፃናት ጥቅም ደህንነት (Best Interest Of The Child) ቅድሚያ ሊሰጠው እንዲገባ ተቀምጧል፡፡ በዚህም መሠረት የጉዲፈቻ ስምምነት እንዲሰረዝ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው በልጁ አኗኗርና አያያዝ እንዲሁም ወደፊት ሕይወቱ ላይ በተጨባጭ የደረሰ ጉዳት መኖሩ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ሊደርስ የሚችል ጉዳት ስለመኖሩ ማረጋገጥ ሲቻል እንደሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶታል፡፡

አመልካቾች በአቤቱታቸው በጉዲፈቻ የተቀበሉት ልጅ ካለበት የጤና ችግር አኳያ ለአስተዳደጉና ለጤንነቱ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ወጪዎችን ለመሸፈን የገንዘብ አቅም የሌላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም ጉዲፈቻ አድራጊዎች ልጁን እንዲወስዱ ቢገደዱ እንኳን ወደፊት ህይወት ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ችግር እንደሚከተል መግለፃቸው ሲታይ ውሉ እንዲቀጥል ማድረጉ የልጁን ጥቅም ህይወቱን አደጋ ላይ መጣል መሆኑን መገንዘብ ስለሚቻል ውሉ አይፈርስም በማለት የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለበት በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ሽሯል፡፡ 

ተጨማሪአስተያየትወይምጥያቄካለዎትያግኙን 

ኢሜይል ፡- [email protected]

አግባብነትያላቸውተጨማሪህግመረጃዎችከማናቸውምኢትዮጵያዊጠበቃ/ህግ ባለሙያ፣ኢትዮጵያዊጉዲፈቻጠበቃ፣ኢትዮጵያዊቤተሰብጠበቃ፣ኢትዮጵያዊፍቺጠበቃ፣ኢትዮጵያዊንብረትጠበቃ፣ኢትዮጵያዊካሳጠበቃ….ማግኘትይችላሉ፡፡

Scroll to Top