የግብር ውሣኔን በመቃወም ይግባኝ ስለማቅረብ መብት

የገቢ ግብር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 የሚያስቀምጣቸውን መረጃዎች ከዚህ እንደሚከተለው እንካፍልዎት፡፡

ምንም እንኳ ብዙም የተለመደና ብዙ ሰው እንደፍትሀብሄር ጉዳይ በብዛት የማይከራከርበት ርዕስ ቢሆንም የግብር አስገቢው ባለስልጣን በሰጠው ውሳኔ ላይ ማናቸውም ግብር ከፋይ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡

በግብር አወሣሠን ቅር የተሠኘ ማንኛውም ግብር ከፋይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች ካሟላ ለግብር ይግባኝ ጉባኤ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡

i. ግብር ከፋዩ አከራካሪ የሆነውን የግብር መጠን አምሣ በመቶ ለግብር አስገቢው ባለስልጣን ሲያስይዝ፣

ii. የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ ለግብር ከፋዩ በደረሠው ወይም በአቤቱታ ኮሜቴ ውሣኔ በተሠጠ በ3ዐ ቀን ውስጥ ይግባኝ ሲያቀርብ፡፡

የግብር ይግባኝ ጉባኤ የሠጠው ውሣኔ በህግ ረገድ ስህተት ነው በማለት ያልተስማማ ማንኛውም ተከራካሪ ወገን የይግባኝ ጉባኤው ውሣኔ በሠጠ በ3ዐ ቀን ውስጥ ጉዳዩን ስልጣን ላለው ፍ/ቤት አቅርቦ ስለ ህጉ ስህተት ፍርድ ሊጠይቅ ይችላል፡፡

ስልጣን የተሠጠው ፍርድ ቤት በህግ የተነሣውን ክርክር ብቻ ተመልክቶ ውሣኔ ከሠጠ በኀላ ጉዳዩን ወደ ጉባኤው ይመልሳል፡፡

በዚህ ስልጣን በተሠጠው ፍ/ቤት በህግ ጥያቄ ላይ በተሠጠው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ ወገን ውሣኔው በተሠጠ በ3ዐ ቀን ውሰጥ ለይግባኝ ሠሚው ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት ይችላል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ሊያይ የሚችለው የመጀመሪያው ፍርድ ቤት በይግባኝ የሚያየውን የህግ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ግብር ከፋዩ በግብር ይግባኝ ጉባኤ የተወሰነበትን ሙሉ ግብር ካልከፈለ በስተቀር የይግባኝ ስሚው ፍርድ ቤት ይግባኙን አይቀበልለትም ፡፡

ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት ያግኙን

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ታክስ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢሚግሬሽን ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፓተንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኮፒራይት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የስራ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ … ማግኘት ይችላሉ፡፡

Scroll to Top