በህዳር 18 ቀን 2001 ዓ.ም የሰበር ውሳኔ የተሰጠበት መዝገብ እንደሚያሳየው ከሆነ መሃይምነትን መሠረት ያደረገ ውል እንዲፈርስ የሚቀርብ አቤቱታ ይርጋ የሚዘጋበት ጊዜ አስር አመት ነው፡፡
ጉዳዩ የተጀመረው አመልካች ባቀረቡት ክስ ሲሆን አቤቱታቸው ላይ እንደተመለከተውም ተጠሪ የወንድሜ ልጅ በመሆኑ ከባለቤቴ ሞት በኋላ አብሮኝ እንዲኖር እቤቴ አስጠግቼው ሲኖር የግል ሃብቴን ለመውሰድ ለመጠቀም አስቦ ነሐሴ 9 ቀን 1984 ዓ.ም እንደማላነና መሃይም መሆኔን በማወቅ የስጦታ ውል አዘጋጅቶ አስፈርሞኛል፡፡ ከዚያም በጥር ወር 1991 ዓ.ም ወደ ቤቴ እንዳልገባ ከልክሎታል ስለዚህም የስጦታው ውል ፈራሽ ነው ተብሎ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡
ተጠሪም በበኩላቸው የስጦታ ውሉ ይሻርልኝ ተብሎ የቀረበው አቤቱታ በፍ/ከ/ሕ/ቁ 181ዐ መሠረት በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ተከራክረዋል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ጉዳዩን ከተመለከተ በኋላ በፍ/ሕ/ሕ/ዩ 181ዐ መሠረት የይርጋ መቃወሚያ ማቅረብ የሚቻለው ውሉ ሲመሰረት የችሎታና የፈቃድ ጉድለት አለበት የሚበልበት ጊዜ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ውሉ እንዲፈርስ የጠየቁት መሃይም ነኝ በማለት ስለሆነ ይህ ደግሞ በዚህ ድንጋጌ ስር ስለማይሸፈን በይርጋ ጠሪ አይሆንም በማለት ወስኗል፡፡
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍ/ቤትም ተጠሪ የስጦታ ውሉ በይርጋ እንዳፈርስ ያቀረቡት አቤቱታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 181ዐ ላይ የተመለከተው የ 2 አመት የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ ስለሆነ የስር ፍ/ቤት በይርጋ ቀሪ አልሆነም ማለቱ አግባብ አይደለም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮትል፡፡
የሰበር ችሎቱም ሁኔታውን እንደመረመረው ከሆነ በግሪ ቀኙ መሃከል ተደርጓል የተባለው ስጦታ ውል እንደመሆኑ መጠን ህጉ ስጦታን አስመልክቶ የተደነገጉት ድንጋጌዎች መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ከስጦታ ውል ድንጋጌዎች አኳያ መርምሮ ለይርጋ ክርክሩ እልባት መስጠት ዘገባው ስለውሎች በጠቅላላው በሚለው ምዕራፍ ስር የተደነገገውን ድንጋጌ መሠረት በማድረግ ውሳኔ መስጠቱ ተገቡነት የለውም፡፡
መሃይምነት ወይም አይነስውርነትን አስመልክቶ የሚፈርም የሙል ይፍረስልን ጥያቄ ከውሉ አፃፃፍ ስርዓት /ፎርም/ ጋር ተያይዞ እንደሚነሳ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1719ና ተከታዮቹ ድንጋጌዎችን መገንዘብ ይዎላል የዚህ አይነተ ይርግም የሚታገደው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 እንዲ በ181ዐ አይደለም፡፡ ይህን በማለትም ችሎተ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰጠው ውሳኔ ድንጋጌው የተሳካ ትርጊም በመስጠት ነው ቢልም ከውጤት አኳያ ግን የሚነቀፍ ስላል የከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሳኔ አፅንቶታል፡፡
ከላይ ከተሰጠው ፍርድ መገንዘብ እንደሚቻለው መሃይምነትን መሠረት በማድረግ ውል እንዲፈርስ የሚቀርብ አቤቱታ አቤቱታው ከፎርም ጋር ተያይዞ ስለሚነሳ ይርጋው የሚታገደው በፍ/ብ/ህ/ቁ 1845 ሲሆን የይርጋው ጊዜም 1ዐ አመት ነው፡፡
ተጨማሪ ጥያቄ አስተያየት ቢኖርዎት ያነጋግሩን ይጠይቁን
ኢሜይል ፡-[email protected]
አግባብነትያላቸውተጨማሪህግመረጃዎችከማናቸውምኢትዮጵያዊጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየንብረትጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየካሳጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊየዉልጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየንብረትጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየካሳጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፍቺ ጠበቃ… ማግኘትይችላሉ፡፡