በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት የተለያዩ ጉዳዮችን ለመፈጸም ሲሄዱ የሚጠየቁትን የማስረጃ ዝርዝሮች ቢያውቋቸው ጊዜ ይቆጥብሎታል ከመንገላታትም ያድኖታል በማለት ከዚህ በታች ለማስቀመጥ ሞክረናል፡፡

1. የንግድ ማህበራት መመሰረቻ ፅሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ለማፅደቅ መሟላት ያለበት

1.1  የአባላቶች መታወቂያ/ፓስፖርት/ ከፎቶ ኮፒ ጋር

1.2  የተዘጋጀ የመመስረቻ ፁሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ከማመልከቻ ጋር

1.3  የማህበሩ ስም አለመያዙን ከንግደና ኢንዱስትራ ሚ/ር ማረጋገጫ /ለጊዜው

1.4  የአክሲዮን ማኀበር ከሆነ የማህበሩን ¼ ካፒታል በዝግ ሂሳብ በማህበሩ ስም ስለመቀመጡ የባንክ ማረጋገጫ

1.5  አባላቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአካል በመቅረብ/በወኪል ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ማሰረጃ ከነፎቶ ኮፒው

1.6  ከአባላቶቹ መካከል የውጭ አገር ዜጋ ካለ የኢንቨስትመንት ፈቃድና በህጋዊ መንግድ ሀገር ውስጥ ስለመግባቱ የሚያረጋግጥ ፖስፖርት ከፎቶ ኮፒ ጋር

1.7  የአገልግሎት ክፍያ ብር 1ዐዐ እና በፈራሚ በየግለሰቡ 1.ዐዐ ብር

2. የንግድ ማህበራት ማሻሻያዎች ቃለ ጉባኤ ለማፅደቅ መሟላት ያለበት

2.1     የአባላቱ መታወቂያ / ፓስፖርት / ከፎቶ ኮፒ ጋር

2.2     የተዘጋጀ የማሻሻያ ቃለ ጉባኤ

2.3    ማሻሻያው የማህበር ስም መለወጥ ከሆነ ስሙ አለመያዙን ከንግደና   ኢንዱስትሪ ሚ/ር ማረጋገጫ / ለጊዜው/

2.4    አባላቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአካል መቅረብ / በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ ከነፎቶ ኮፒው/

2.5     የአገልግሎት ክፍያ ብር 5ዐ.ዐዐ በፈራሚው በየግለሰቡ 1.ዐዐ ብር

3. የግለሰብ ነጋዴ የዋና ምዝገባ መሟላት ያለበት

3.1      የግብር ከፋይነት መለያ /TIN/ ሠርተፊኬት ከፎቶ ኮፒ ጋር

3.2      ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው ከሆነ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ከፎቶ ኮፒ ጋር

3.3       ዕድሜው 18 ዓመት ያልሞላው ከሆነ የፍ/ቤት የሞግዚትነት

     ማረጋገጫና የሞግዚቱ መታወቂያ /ፓስፖርት / ከፎቶ ኮፒ ጋር

3.4       የቅርብ ጉዜ 2 ጉርድ ፎቶ ግራፍ

3.5       በውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ከፎቶ ኮፒ ጋር

3.6       የውጪ አገር ዜጋ ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድና በህጋዊ መንግድ አገር ውስጥ ስለመግባቱ ፓስፖርት ከፎቶ ኮፒ ጋር

3.7      ተሞልቶ የተፈረመ ማመልከቻ ቅፅ / ቅፁ በቢሮው ተዘጋጅቷል /

3.8      የአገልግሎት ክፍያ ብር 1ዐዐ.ዐዐ

4. ለንግድ ማህበር ዋና ምዘገባ ለመካሄድ መሟላት ያለበት

4.1   የፀደቀ የመተዳደሪያ ደንበና መመስረቻ ፅሁፍ

4.2   የሰራ አስኪያጁ መታወቂያ /ፓስፓርት/ ከፎቶ ኮፒ ጋር

4.3    የስራ አስኪያጁ ወይም ህጋዊ ወኪሉ  / በወኪል / ከሆነ ሕጋዊ የውክልና  

      ማስረጃ ከነፎቶ ኮፒው/

4.4   ተሞልቶ የተፈረመ ማመልከቻ ቅፅ / ቅፁ በቢሮው ተዘጋጅቷል/

4.5   የአገልግሎት ክፍያ ብር 2ዐዐ.00

5. የግለስብና የግንድ ማህበር አጭር ምዝገባ ለመስጠት መሟላት ያለበት

5.1  የዋና ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከፎቶ ኮፒ ጋር

5.2  የግለሰቡ ወይም ማህበር  ከሆነ የሰራ አስኪያጁ የቅርብ ጊዜ 2 ጉርድ ፎቶ     ግራፍ ከመታወቂያና ከፎቶ ኮፒ ጋር

5.3  ማኀበር ከሆነ የመመስረቻ ፁሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ከፎቶ ኮፒ ጋር

5.4   በወኪል ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ከፎቶ ኮፒ ጋር

5.5   ተሞልቶ የተፈረመ የማመልከቻ ቅጽ / ቅፁ በቢሮው ተዘጋጅቷል/

5.6    የአገልግሎት ክፍያ ብር 1ዐዐ.00/በማህበር 200.00 ብር

6. የምዝገባ ማሻሻያ ለግለሰብ ነጋዴ መሟላት ያለበት

ሀ/ የባለቤትነት ለውጥ በሰጦታ፣ በውርስ ፣ በሽያጭ ሲከናወን መሟላት ያለበት

6.1   ከግብር ነፃ ስለመሆኑ ክሊራንስ

6.2  መታወቂያ / ፓስፖርት / ከፎቶ ኮፒ ጋር

6.3   የቅርብ ጊዜ 4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ

6.4    የውርስ ከሆነ የፍ/ቤት የወራሽነት ማስረጃ ከፎቶ ኮፒ ጋር

6.5    በስጦታ ወይም በሽያጭ ከሆነ በሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት የፀደቀ ውል  

      እና ውሉ ለሶስተኛ ወገን እንዲያውቀው የተደረገበት የጋዜጣ ማስታወቂያ

6.6   በውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ከፎቶ ኮፒ ጋር

6.7  የቀድሞው የምዝገባ ምስክር ወረቀት

6.8   ተሞልቶ የተፈረመ ማመልከቻ ቅፁ /ቅፁ በቢሮው ተዘጋጅቷል/

6.9  የአገልግሎት ክፍያ ር 1ዐዐ.ዐዐ

ማስታወሻ ፡- ይህ አገልግሎት የሚሰጠው የቀድሞው ፋይል በሚገኝበት ክፍለ ከተማ ወይም ቀበሌ ነው፡፡

ለ. ሌሎች ለውጦች

7. / የንግድ ማህበርን ጨምሮ የአላማ፣ የስራ አስኪያጅ፣ የአድራሻ፣

     የካፒታል ወዘተ  ለውጥ /

7.1   የቀድሞው የምዘገባና የፈቃድ ስርተፊኬት

7.2   ማኀበር ከሆነ በአባላት የፀደቀ ቃለ ጉባኤ

7.3  የግለስቡ ወይም ማህበር ከሆነ የስራ አስኪያጁ የቅረብ ጊዜ 4 ጉርድ    ፎቶ ግራፍ

7.4  በውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስርጃ ከፎቶ ኮፒ ጋር

7.5   ተሞልቶ የተፈረመ የማመልከቻ ቅጹ /ቅፁ በቢሮው ተዘጋጅቷል/

7.6  የአገለግሉት ክፍያ ለግለስብ ብር 1ዐዐ.ዐዐ ለማህበር ብር 2ዐዐ.ዐዐ

8. የግለሰብ የዋና ምዝገባ ስረዛ መሟላት ያለበት (የቀድሞው ፋይል  

   ከሚገኝበት ክ/ከተማ ወይም ቀበሌ )

8.1  ከግብር ነፃ ስለመሆኑ ክሊራንስ

8.2  በግለስቡ ወይም በወኪሉ የተፃፈ ማመልከቻ

8.3  በውክልና ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃና መታወቂያ ከፎቶ ኮፖ ጋር

8.4  የምዝገባው ምስክር ወረቀት

8.5  የአገልግሎት ክፍያ ብር 1ዐዐ.ዐዐ

9.  የንግድ ስራ ፈቃድ ለመመለስ መሟላት ያለበት(የቀድሞ ፋይል ከሚገኝበት ክ/ከተማ   ወይም ቀበሌ)

9.1     ከግብር ነፃ ስለመሆኑ ክሊራንስ

9.2     በግለሰቡ ወይም በወኪሉ የተፃፈ ማመልከቻ

9.3     በውክልና ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃና መታወቂያ ከፎቶ ኮፖ ጋር

9.4     የአገልግሎት ክፍያ ብር 1ዐዐ.ዐዐ

10.   ለአዲስ የንግድ ስራ ፈቃድ ለማውጣት መሟላት ያለበት

10.1   የንግድ ማህበር ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ /TIN/ ሰርተፊኬተ ከፎቶ   

       ኮፒ ጋር

10.2   የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት

10.3   የግለሰቡ ወይም ማኀበር ከሆነ የስራ አስኪያጁ የቅርብ ጊዜ 2 ጉርድ

      ፎቶ ግራፍ

10.4  በውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ከፎቶ ኮፒ ጋር

10.5  የንግድ ሰራ መስኩ የሙያ ብቃት የሚጠይቅ ከሆነ ከሚመለከተው

     መሰሪያ ቤት የብቃት ማረጋገጫ ወይም መስፈርት የወጣለት ከሆነ  

     መስፈርቱን ስለማሟላቱ የአመልካች ማረጋገጫ

10.6  ተሞልቶ የተፈረመ ማመልከቻ ቅጽ /ቅፁ በቢሮው ተዘጋጅቷል፡፡

10.7  የአገልግሎት ክፍያ ብር 1ዐዐ.ዐዐ/ለማህበር 200.00 ብር

11.           ለንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት ማሟላት ያለበት

11.1 የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ክሊራንስ

11.2 የንግድ ፈቃድ

11.3 በውክልና ከሆነ የውክልና ማስርጃ ከፎቶ ኮፒ ጋር

11.4 ተሞልቶ የተፈረመ የማመልከቻ ቅጽ/ ቅፁ በቢሮው ተዘጋጅቷል/

11.5  የአገልግሎት ክፍያ ለግለሰብ ብር 1ዐዐ.ዐዐ ለማህበር ብር 2ዐዐ.ዐዐ


12.   
ለንግድ ምዘገባና ፈቃድ መረጃ መሟላት ያለበት

12.1 የባለጉዳይ ወይም የሕጋዊ ወኪል ማመልከቻ

12.2 የአገልግሎት ከፍያ ብር 1ዐዐ.ዐዐ  

 ተጨማሪ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት  ያግኙን

አግባብነት ያላቸው ተጨማሪ ህግ መረጃዎች ከማናቸውም ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የኢንቨስትመንት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንብረት ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የወንጀል ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የካሳ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የፍቺ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ የንግድ ምልክት ጠበቃ፣ … ማግኘት ይችላሉ፡፡