ጉዳዩ የተጀመረው ተጠሪ በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ አካባቢ የመንገድ ስራ ሊያከናውን በአመልካች ንብረት ላይ ግምቱ ብር 25,569.85 የሆነ ጉዳት ማድረሱን ገልፆ ይህንኑ ገንዘብ ከነወለዱና ወጪው ጋር እንዲተካ እንዲወሰንለት በመጠየቁ ነው፡፡

ተጠሪም በሰጠው መልስ ተከሳሽ ድርጅት በግሪክ ሀገር ህግ መሠረት የተቋቋመና አድራሻውም በአቴንስ በመሆኑና በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ አለመመዝገቡን ገልፆ ጉዳዩ በየትኛው ፍ/ቤት ይታያል የሚል የግል አለም አቀፍ ህግ ስለሚያስነሳ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን የለውም የሚል መቋወሚያ አንስቶ ተከራክሯል፡፡ ፍ/ቤቱም ይህንን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በመቀበል ፍ/ቤቱ ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን የለውም ሲል ክሱን ዘግቷል፤ ጉዳዩም የሰበር ችሎት ደርሶ ታይቷል፡፡

ችሎቱም እንደተመለከተው ለክሱ ምክንያት የሆነውን ጉዳት ያደረሰው ስራውን በኢትዮጵያ ውስጥ ሲያከናውን መሆኑን ክሱ የቀረበውም ጉዳቱ በደረሰበትና ንብረቱ በሚገኝበት ክልል የሚገኘው ፍ/ቤት መሆኑን ነው፡፡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 27(1) መሠረትም የገንዘብ መጠኑን መሠረት አድርጐ የሚወሰነው የስረ-ነገር ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ጉዳቱ በደረሰበትና ንብረቱ በሚገኝበት ክልል በሚገኘው ፍርድ ቤት ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን ማብራሪያ በመስጠት የሰበር ሰሚው ችሎት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በመሻር አንድ ተከሳሽ ድርጅት በውጭ ሀገር ህግ መሠረት የተቋቋመ የንግድ ድርጅቶች ቢሆንም ከውል ውጭ በሆነ ግንኙነት በኢትዮጵያ ፍ/ቤት ቀርቦ ሊዳኝ የሚችልና የፌደራሉ መጀመሪያ ፍ/ቤት ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን ያለው መሆኑን ገልጿል፡፡

ኢሜይል [email protected]

አግባብነትያላቸውተጨማሪህግመረጃዎችከማናቸውምኢትዮጵያዊጠበቃ፣ኢትዮጵያዊታክስጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየቤተሰብጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየወንጀልጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየንብረት/ውርስጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየካሳጠበቃ፣ኢትዮጵያዊፍቺጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየጉዲፈቻ ጠበቃ … ማግኘትይችላሉ፡፡