በፍ/ብ/ስ/ህ/ቁ. 33(2) በግልፅ አንድ ሰው ክስ ከማቅረቡ በፊት ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባው ተደንግጓል፡፡
ታዲያ ይህ ማለት በግልግል ዳኝነት አንድ ጉዳይ ለመፍታት ከተስማሙ ወገኖች አንዱ ይህንን ግዴታውን ያፈረሰ እንደሆነ ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ያለውን ጥቅም ማሳየት አይችልም ተብሎ መዝገቡ ይዘጋል ማለት ነው?
በህዳር 1 ቀን 2003 ዓ.ም በመ.ቁ 56368 የዋለው ችሎት ይህንን የተመለከተ ነበር፡፡ ጉዳዩ በአመልካችና በተጠሪ በተደረገው ውል መሠረት የግልግል ዳኛ በፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዲመረጥ አመልካች ያቀረበውን ጥያቄ የሚመለከት ነው፡፡
ይህ ጉዳይ በስር ፍ/ቤቶች ታይቶ ተጠሪ ተጠርቶ መልስ እንዲሰጥ ከመደረጉ በፊት ጥያቄው በፍ/ቤት የሚስተናገድ አይደለም በማለት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 231 በመጥቀስ ዘግተውታል፡፡ ጉዳዩን የሰበር ችሎት ደርሶ ተመርምሯል፡፡
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 1731 መሠረት በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ውሎች ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ሕግ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሳሽ የሆነው ወገን ተጣሰብኝ የሚለውን መብት ለማስከበር ዳኝነት የሚጠይቀው የመብቱን ምንጭ ወይም መሠረት ውል ወይም ህግ እንደሆነ ለማረጋገጥ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 33(2) ም ከሳሽ ከተከሳሽ ላይ የሚጠይቀው ጥቅም ወይም መብት በማረጋገጥ አቤቱታውን ያቀርብ ዘንድ ይጠበቅበት ቢባልም የመብቱ መሠረት ሕግ ወይም ውል መሆኑን በግልፅ ማሳየት አለበት ማለት ነው፡፡
ከላይ የተዘረዘረውን ማብራሪያ በመስጠት በክሉ ላይ የተነሳው ጉዳይ የክስ ምክንያት የለውም የሚባል አይደለም በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ሽሯል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ውሳኔ መረዳት የሚቻለው በውል የተመሠረተን ግዴታ እንዲፈፀም የሚቀርብ ማናቸውም አቤቱታ በፍ/ቤቶች ሊስተናገድ እንደሚገባ ነው፡፡
ተጨማሪአስተያየትወይምጥያቄካለዎትያግኙን፡፡
ኢሜይል ፡- [email protected]
አግባብነትያላቸውተጨማሪ የህግመረጃዎችከማናቸውምኢትዮጵያዊጠበቃ፣ኢትዮጵያዊታክስጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየቤተሰብጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየወንጀልጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየንብረት/ውርስጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየካሳጠበቃ፣ኢትዮጵያዊፍቺጠበቃ፣ኢትዮጵያዊየጉዲፈቻ ጠበቃ … ማግኘትይችላሉ፡፡