ከ500.00 (አምስት መቶ) ብር በላይ በአደራ ስለመሰጠቱ በምስክር ማስረዳት ይቻላል?

የፍ/ብሔር ግንኙነት በሚቋቋምበት ጊዜ ይህ ግንኙነት ክርክር ቢያስነሳ ተከራካሪዎች የሚለያዩባቸውን ነጥቦችን ለማስረዳት መቅረብ ያለበት ማስረጃ በህጉ የተወሰነ ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ የፍ/ብሔር ግንኙነቶች ክርክር ሲያስነሱ በምስክር ወይም በተለየ ማስረጃ መረጋገጥ ያለባቸው መሆኑ በህግ ተለይተው ተመልክተዋል፡፡ የገንዘብ አደራን በተመለከተ ሊቀርብ የሚገባውን የማስረጃ አይነት በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2472 ላይ የተቀመጠ ሲሆን በዚህም መሠረት ለአደራ ተቀባዩ የተሰጠው እቃ ጥሬ ገንዘብ የሆነ […]

በግልግል ዳኝነት እንዲፈታ በውል የተቀመጠን ግዴታ ለማስፈፀም የሚቀርብ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም ማለት ይቻላል?

በፍ/ብ/ስ/ህ/ቁ. 33(2) በግልፅ አንድ ሰው ክስ ከማቅረቡ በፊት ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባው ተደንግጓል፡፡ ታዲያ ይህ ማለት በግልግል ዳኝነት አንድ ጉዳይ ለመፍታት ከተስማሙ ወገኖች አንዱ ይህንን ግዴታውን ያፈረሰ እንደሆነ ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ያለውን ጥቅም ማሳየት አይችልም ተብሎ መዝገቡ ይዘጋል ማለት ነው? በህዳር 1 ቀን 2003 ዓ.ም በመ.ቁ […]

በውጭ ሀገር ህግ መሠረት የተቋቋመ የንግድ ድርጅቶች ከውል ውጭ በሆነ ግንኙነት በኢትዮጵያ ፍ/ቤት ቀርቦ ሊዳኝ ይችላል፡፡

ጉዳዩ የተጀመረው ተጠሪ በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ አካባቢ የመንገድ ስራ ሊያከናውን በአመልካች ንብረት ላይ ግምቱ ብር 25,569.85 የሆነ ጉዳት ማድረሱን ገልፆ ይህንኑ ገንዘብ ከነወለዱና ወጪው ጋር እንዲተካ እንዲወሰንለት በመጠየቁ ነው፡፡ ተጠሪም በሰጠው መልስ ተከሳሽ ድርጅት በግሪክ ሀገር ህግ መሠረት የተቋቋመና አድራሻውም በአቴንስ በመሆኑና በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ አለመመዝገቡን ገልፆ ጉዳዩ በየትኛው ፍ/ቤት ይታያል የሚል የግል […]

በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት የተለያዩ ጉዳዮችን ለመፈጸም ሲሄዱ የሚጠየቁትን የማስረጃ ዝርዝሮች

በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት የተለያዩ ጉዳዮችን ለመፈጸም ሲሄዱ የሚጠየቁትን የማስረጃ ዝርዝሮች ቢያውቋቸው ጊዜ ይቆጥብሎታል ከመንገላታትም ያድኖታል በማለት ከዚህ በታች ለማስቀመጥ ሞክረናል፡፡ 1. የንግድ ማህበራት መመሰረቻ ፅሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ለማፅደቅ መሟላት ያለበት 1.1  የአባላቶች መታወቂያ/ፓስፖርት/ ከፎቶ ኮፒ ጋር 1.2  የተዘጋጀ የመመስረቻ ፁሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ከማመልከቻ ጋር 1.3  የማህበሩ ስም አለመያዙን ከንግደና ኢንዱስትራ ሚ/ር ማረጋገጫ /ለጊዜው 1.4  […]

በውል ውስጥ የስራን ግዴታ ሳይወጡ ሌላው ወገን ግዴታን አልተወጣም የሚል ክስ ማቅረብ ይችላል?

በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1757 ላይ በግልፅ እንደተደነገገው አንድ ውል እንዱፈፀምለት የ+ሚጠይቅ አካል መጠየቅ የሚችለው በውሉ መሠረት አስቀድሞ ሲወጣው የሚገባግዴታ ካለ ይህንን ግዴታ ከተወጣ በኋላ መሆኑን ነው፡፡  በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተጀመረ ክርክርም ይህን የሳያል ጉዳዩ የነበረው በከሳሽ ወኪል በኩል ለተከሳሽ በብር 50,000 ብር የሰጡላቸው መሆኑን ለቅድሚያም 19,000 ብር ከፍለውኝ መኪናውን አስረክቤያቸዋለሁ፡፡ ነገር ግን ጠሪውን 31,000 […]

በወንጀል ክስ ተከሶ ነፃ መውጣት በራሱ አንድን ሠራተኛ ወደ ቀድሞው ስራው ለመመለስ መብትን ይሰጣል?

አንድ ባለጉዳይ በአቃቤ ህግ በኩል የአሠሪና ሠራተኛን ግንኙነት በተመለከተ የተመሠረተ የወንጀል ክስ ላይ ነፃ በመውጣቱ ብቻ ወደ ቀድሞው ስራዬ ልመለስ ሌሎች ክፍያዎችም ሊከፍሉኝ ይገባል ማለት አይችልም፡፡  ይህ የሆነበት ምክንያትም በመሰረቱ የወንጀል ክስና የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅን መሠረት አድርጎ የሚቀርብ ክስ የተለያየ ይዘትና አላማ ያላቸው ከመሆኑም በላይ በማስረጃ አመዛዘን ረገድም የተለያዩ መርሆችን መሠረት የሚያደርጉ መሆናቸው ነው፡፡ በህዳር […]

በባህላዊ ሆነ ሀይማኖታዊ ስርዓት የተፈጸመ ጋብቻ በክብር መዝገብ ሹም ፊት እስከሚመዘገብበት ጊዜ ድረስ የሚኖረው ህጋዊ ውጤት ምንድን ነው?

ሕጉ በሚፈቅደው የጋብቻ አፈፃፀም ስርአት መሠረት የተፈፀመ ጋብቻ በክብር መዝገብ ሹም ፊት እስከሚመዘገብበት ጊዜ ድረስ ላሉት ጊዜያቶች ህጋዊ ውጤት ሊኖረው ይችላል ወይ? በዚህ ጊዜያት ውስጥ በህጉ ላይ የባልና ሚስት መብትና ግዴታ ተብለው የተገለፁት በእነዚህ ተጋቢዎች ላይ ተፈፃሚ ሊሆን ይችላል ወይስ አይችልም? በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 28(1) ላይ ጋብቻው የተፈፀመው በማንኛውም የጋብቻ አፈፃፀም ስርዓት ቢሆንም አግባብ […]

መሃይምነትን መሠረት በማድረግ ውል እንዲፈርስ የሚቀርብ አቤቱታ በ1ዐ አመት ጊዜ ውስጥ በይርጋ ይዘጋል?

በህዳር 18 ቀን 2001 ዓ.ም የሰበር ውሳኔ የተሰጠበት መዝገብ እንደሚያሳየው ከሆነ መሃይምነትን መሠረት ያደረገ ውል እንዲፈርስ የሚቀርብ አቤቱታ ይርጋ የሚዘጋበት ጊዜ አስር አመት ነው፡፡  ጉዳዩ የተጀመረው አመልካች ባቀረቡት ክስ ሲሆን አቤቱታቸው ላይ እንደተመለከተውም ተጠሪ የወንድሜ ልጅ በመሆኑ ከባለቤቴ ሞት በኋላ አብሮኝ እንዲኖር እቤቴ አስጠግቼው ሲኖር የግል ሃብቴን ለመውሰድ ለመጠቀም አስቦ ነሐሴ 9 ቀን 1984 ዓ.ም […]

ሕጋዊ ፎርማሊቲውን የጠበቀ እና በፍ/ቤት የፀደቀ ኑዛዜ ዋጋ አልባ (ኑዛዜ) ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ አለ ወይ?

በፍ/ብ/ሕ አንቀጽ 665(2) መሠረት “የኑዛዜ ቃል አፈፃፀሙም የማይቻል እንደሆነ እንደዚሁ ፈራሽ ነው፡፡” በማለት የደነገገ ሲሆን ይህን ነጥብ አስመልክቶም ሰበር ሰሚ ችሎት የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ጉዳዩ በስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበው በአሁኑ አመልካች ሲሆን ጥያቄያቸውም፤ ሟች ባላምባራስ ዘውዴ ደምሴ በመስከረም 26/1984ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በፍ/ቤት ፀድቆላቸው የኑዛዜ ወራሽነታቸው ተረጋግጦ እንደሰጣቸው ነው፡፡ ተጠሪዎቹ በተቃዋሚነት ቀርበው አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች […]

Will the Contract of employment cease when the particular project ends?

As stipulated under article 10(C) of Proclamation no 377/96 an irregular work relating to permanent part of the work of an employer but performed on an irregular interval is considered to be a contract of employment for a definite period of time. So, any employee working in a company for a specific project, the contact […]